Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dhcd

Department of Housing and Community Development
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about DHCD services for Amharic speakers.

የመሥሪያ ቤቱ ስም:  የቤቶች እና የማህበረሰብ ልማት መምሪያ 

ተልዕኮ:

የቤቶች እና የማህበረሰብ ልማት መምሪያ (DHCD) ተልዕኮ ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ ቤቶችንና የኢኮኖሚ ልማት ዕድሎችን መፍጠርና ማቆየት እንዲሁም በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ በቂ በሆነ ሁኔታ አገልግሎት ያልደረሳቸውን ማህበረሰቦች ማጠናከር ነው።  

ዋና ፕሮግራሞች/የክፍሎች ገለጻ

የልማት ገንዘብ –  ዋጋቸው መጠነኛ የሆነ ቤቶችን መገንባትና ማቆየት ለDHCD አስፈላጊ ነው። ስለሆነም የኮሎምቢያ ዲስትሪክት አካባቢዎችን የሚያገለግሉ የኪራይ፣ የመኖሪያ ቤት እና የማህበረሰብ ህንጻዎችን ለማስፋፋት በገንዘብ ልማት ክፍል በኩል እና ክፍሉ በሚያወጣው ዓመታዊ የዕቅድ ጥያቄ ማቅረቢያ (RFP) የሚገኝ ገንዘብ አለ።
የቤት ባለቤትነት እና የቤቶች እደሳ – DHCD በማህበረሰበ ድርጅቶች (CBO) አማካኝነት ስለቤቶች የማማከር፣ በባንክ በዕዳ ምክንያት ቤት እንዳይወሰድ መከላከል፣ ሌድ ባለው የቤቶች ቀለም ምክንያት የሚመጡ አደጋዎችን መለየትና መቆጣጠር፣ ለአነስተኛ ንግዶች የቴክኒክ ድጋፍ እና የህንጻዎችን ገጽታ ማሻሻል የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ይሰጣል።  በተጨማሪም DHCD ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ለሚገዙ፣ አነስተኛ እና መለስተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች እና ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት መንግሥት ሠራተኞች የቤት ባለቤትነትና የቤት እደሳ አገልግሎቶችን  በሚከተሉት በተለያዩ የዲስትሪክት ፕሮግራሞች ይሰጣል፦ ለሁሉም የዲስትሪክት ነዋሪዎች የሚሰጥ የቤት ግዥ ዕርዳታ ፕሮግራም (HPAP)፣  ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት መንግሥት ሠራተኞች የሚሰጥ በቀጣሪ የሚታገዝ የቤቶች ፕሮግራም (EHAP) እንዲሁም በሠራተኛ የገቢ መጠን ድርድር የቤት ግዥ ፕሮግራም (NEAHP) መስፈርቱን ለሚያሟሉ የሠራተኞች ማህበር ዓባላት በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የመኖሪያ ቤት ለመግዛት የገንዘብ ዕርዳታ ይሰጣል። የቤት ባለቤትነትን ለማቆየት DHCD ጤናን፣ ደህንነትን እና የግንባታ ኮድ መተላለፎችን በተመለከተ ዕርዳታና ብድር ይሰጣል።   
የቤቶች እና ኮንዶሚኒየም ህግ – በዚህ ፕሮግራም ስር ክፍያቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች (ADUs)፣ የኮንዶ እና የህብረት ቤቶች ልዋጭ እና ሽያጭ፣ የቤቶች አቅራቢ እንባ ጠባቂ፣ የቤቶች መረጃ ማዕከል፣ ሁሉን የሚያካትት የክልል (IZ)፣ የኪራይ ቁጥጥር፣ እና የኪራይ ቤቶች ኮሚሽን ይካተታሉ። 

አገልግሎቶች:

የማህበረሰብ ህንጻዎች ገንዘብ ዕርዳታ

የDHCD የገንዘብ ልማት ክፍል የኮሎምብያ ዲስትሪክት አካባቢዎችን የሚያገለግሉ የማህበረሰብ እና የንግድ ህንጻዎችን ለማሳደግ የገንዘብ ዕርዳታ ይሰጣል።  እነኝህ ህንጻዎች የቢሮ ህንጻዎችን፣ ክሊኒኮችን፣ የመዋእለ ህጻናት እና የመዝናኛ ማዕከሎችን ያካትታሉ።    ገንዘቡ የገንዘብ ዕርዳታ ዕቅድ በማቅረብ ለትርፍ ለማይሠሩ ድርጅቶች እና ለትርፍ ለማይሠሩ መጠነኛ ዋጋ ቤቶችን ለሚገነቡ ድርጅቶች ይሰጣል።  

የተከራይ ቤት የመግዛት ዕርዳታ እድል  - ተከራዮች የአፓርትመንት ህንጻው በመሸጡ ምክንያት እንዲለቁ የሚደረጉ ከሆነ DHCD ዕርዳታ ይሰጣቸዋል። የተከራዮች ቡድን የአፓርትመንት ህንጻውን ለመግዛት እና ወደፊት ወደ የሕብረት ቤት ወይም ኮንዶሚንዬም ለመለወጥ ካሰቡ DHCD የገንዘብ እና የቴክኒካል እርዳታ ይሰጣቸዋል።  በተጨማሪም የተከራዮች ቡድን የአፓርትመንት ህንጻውን ለመግዛት እና ወደፊት ወደ የሕብረት ቤት ወይም ኮንዶሚንዬም ለመለወጥ ካሰቡ DHCD የተለየ ነጻ የድርጅታዊ እና የአሠራር አገልግሎቶች ይሰጣቸዋል።  አገልግሎቶቹ የተከራዮች ማህበር ማቋቋም ዕርዳታ፣ የህግ ሰነዶችን ማዘጋጀት እና የብድር ማመልከቻዎችን የማዘጋጀት ዕርዳታዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ።

ኮንዶ እና የሕብረት ቤቶችን ማደስ እና መሽጥ

በማደስ ድንጋጌ (የ1980 የኪራይ ቤቶችን የማደስ እና የመሸጥ ድንግጋጌ) መሠረት የዲስትሪክቱ ኗሪዎች በተከራይነት የሚኖሩበት ኮንዶ/የመኖሪያ ቤት ለሽያጭ ከቀረበ ‘የመግዛት መብት ዕድል’፣ ‘የተከራይ የመቃወም የመጀመሪያ መብት’፣ ‘የሽያጭ ማስታወቂያዎችን የመቀበል’ መብት፣ ‘ንብረቱ ወደ የማሕበር ቤት ወይም ወደ ኮንዶ መቀየር’ ማስታወቂያዎችን የማግኘት መብት አላቸው።  በኮንዶሚንዬም ድንጋጌ (በተሻሻለው የ1976  የኮንዶሚንዬም የቴክኒካል እና የማብራራት ማሻሻያ ድንጋጌ) መሠረት አንድ ህንጻ ሠሪ ዩኒቶቹን ለመግዛት ፍላጎት ላላቸው ገዢዎች ዕድል ከመስጠቱ በፊት እና የተቋም ብልሽት ዋስትና  ፕሮግራም ከማድረጉ በፊት ኮንዶሚንዬም ዩኒቶችን ከመሥራት እና ከማስመዝገብ ያግዳል።   

የቤት ክፍያ ዕርዳታ ፕሮግራም

የአፓርትመንቱ ህንጻ ወደ ኮንዶሚንዬም ወይም ወደ የሕብረት ቤቶች በመለወጡ ምክንያት የተፈናቀሉ ተከራዮች የገንዘብ ዕርዳታ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።    ተከራዮች ብቁ ለመሆን አስፈላጊ ሁኔታዎች እዚህ ተዘርዝረዋል። 

የቤት አቅርቦት እምባ ጠባቂ (ተከራካሪ) - የቤት አቅርቦት እምባ ጠባቂ (HPO) አነስተኛ ቤቶች ለሚያከራዩ (አከራዮች) ሰለ የኮሎምብያ ዲስትሪክት የቤት ህጎች በተሻለ መንገድ እንዲያውቁ ይረዳል።    HPO የቤቶች ድንጋጌ አስተዳደር ማስታወቂያዎችን፣ አቤቱታዎችን እና ሌላ ቅጾችን የመግለጽ ዕርዳታ ይሰጣል፣ ትምህርት እና ሕብረተሰቡን የመድረስ አገልግሎት ይሰጣል፣ የሚሰነዘሩ ትችቶችን፣ ጥያቄዎችንና አቤቱታዎችን ያዳምጣል፣ ስለኪራይ ቁጥጥር፣ የተከራይ ቤት የመግዛት ዕድል እና ስለ መሸጥ እና መለወጥ ቴክኒካል ዕርዳታ ይሰጣል፣ አከራይ እና ተከራይን የመሚመለከቱ መረጃዎችን ይሰጣል፣ እንዲሁም የትናንሽ ቤቶች አከራዮችን ወደ የሚመለከታቸው ቡድኖች ይመራል።  

የቤቶች መረጃ ማዕከል  - በ1800 Martin Luther King, Jr. Avenue, SE, Washington, DC 20020 በአንደኛው ፎቅ ላይ የሚገኘው የመረጃ ማዕከል ለተከራዮች እና ለአከራዮች ስለ ኤጀንሲው ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች መረጃ ይሰጣል። የመረጃ ማዕከሉን በስልክ ቁጥር (202) 442-9505 ማነጋገር ይቻላል።  የDHCD መረጃ ማዕከል ከሰኞ እስክ ዓርብ ከ8:30 am – 3:30 pm ክፍት ነው።   በተጨማሪም ኗሪዎች DCHousingSearch.orgን ከDHCD የመረጃ ማዕከል ማግኘት ይችላሉ።  DCHousingSearch.org በኮሎምብያ ዲስትሪክት ውስጥ ቤት ለማግኘት ያለውን እድል ዝርዝር የሚያቀርብ ነጻ የመረጃ አገልግሎት ነው። 

የኪራይ ቤቶች ኮሚሽን

DHCD የተሻሻለውን የ1985 የኪራይ ቤቶች ድንጋጌን በማስከበር ምርጥ የሆኑ መጠነኛ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን በማቆየት እና ቁጥራቸውን በመጨመር የዲስትሪክቱን ኗሪዎች ያገለግላል።   የኪራይ ቤቶች ኮሚሽን ራሱን የቻለ ሕጋዊ የሆነ የኪራይ ቤቶችን ድንጋጌ የሚያስከብር ክፍል ነው።  ድንጋጌውን ለማስከበር የሚያገለግሉ ህጎችን የማውጣት፣ የማሻሽል እና የመሻር ኃላፊነት አለው፣  የዓመቱን አጠቃላይ የኪራይ እና/ወይም የኪራይ ጣርያ የኮሎምብያ ዲስትሪክት በሚገኝበትን አካባቢ የተጠቃሚ የዋጋ መለኪያ ዓመታዊ ለውጦች (ካሉ)ማስተካከያ አረጋግጦ ያሳትማል። እንዲሁም አከራይን ወይም ሌሎች የሚመለከታቸው ኗሪዎችን የተመለከቱ በኪራይ አስተዳዳሪ እና የአስተዳደር ችሎት ቢሮ (OAH) የሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፤ የኪራይ ቤቶች ኮሚሽን አድራሻ፦ 441 4th Street NW, Suite 1140B North, ስልክ ቁጥር (202) 442-8949.

ሁሉን ክልል ያካተተ የመጠነኛ ዋጋ ቤቶች ፕሮግራም  – አስር ወይም ከአስር  በላይ ያላቸው አዳዲስ የመኖርያ ቤቶች ሥራ ፕሮጀክቶች እንዲኖር፣ እና  አሁን ያሉ ህንጻዎችን በሀምሳ ፐርሰንት ወይም በላይ የሚያስፋፉ የእደሳ ፕሮጀክቶች፣ እና  አስር ወይም ከአስር በላይ የሚሆኑ መጠነኛ ዋጋ ያላቸው የመኖሪያ ክፍሎችን በመኖያ አካባቢ እንዲጨመሩ ያደርጋል።   ሁሉን ያካተተ መጠነኛ ዋጋ ቤቶች ፕሮግራም ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተስቦች በዲስትሪክቱ ውስጥ መጠነኛ ዋጋ ያላቸው ቤቶች እንዲከራዩ ወይም እንዲገዙ ዕድል ይሰጣቸዋል።  በፕሮግራሙ ለመካፈል ብቁነታቸውን ለማወቅ ቤተስቦች በDHCD መጠነኛ ዋጋ የመኖሪያ ቤቶች ማፈላለጊያ ድህረ ገጽ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።  እያንዳንዱ በፕሮግራሙ ተሳታፊ ፈቃድ በተሰጠው የማህበረስብ ድርጅት በሚሰጥ የቤት ምክር ሥልጠና መሳተፍ አለበት።  ምዝገባውን ከጨረሱ በኋላ፣ ብቁ የሆኑ ቤተስቦች በቤቶች ሎተሪ እንዲሳተፉ ይፈቀድላቸዋል።  በዲስትሪክቱ ለሚኖሩ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።  

የኪራይ ቁጥጥር

የተሻሻለው የ1985 የኪራይ ቤቶች ድንጋጌ በኮሎምብያ ዲስትሪክት ለሚገኙ የኪራይ ቤቶች የሚሠራ እና ተከራዮችን ከማባረር ጥበቃ የሚሰጥ የኪራይ ቁጥጥር ህግ ነው።    በተጨማሪም ድንጋጌው ለማንኛውም ከኪራይ ቁጥጥር ውጭ ላልሆኑ የኪራይ ቤቶች የኪራይ ተመጣጣኝነት ይሰጣል።  ሁሉም የኪራይ ቤቶች በDHCD የኪራይ መኖርያዎች ክፍል በኪራይ ቁጥጥር ወይም ከቁጥጥር ውጭ በመሆን መመዝገብ አለባቸው።  ማንኛውም ያልተመዘገበ ዩኒት የኪራይ ቁጥጥር ይኖርበታል።  ከኪራይ ቁጥጥር ውጭ ለመሆን የሚከተሉት መኖር አለባቸው፦ ዩኒቱ በፌደራል ወይም በዲሳትሪክቱ የሚረዳ መሆን፣ ከ1975 ዓ.ም. በፊት የተሠራ፣ ባለቤቱ በዲስትሪክቱ ውስጥ ከአራት በላይ የኪራይ ቤቶች የሌለው ግለ ሰብ (ድርጅት ያልሆነ) መሆን አለበት፣ እና/ወይም ድንጋጌው በሥራ ላይ በዋለበት ጊዜ ባዶ የነበረ መሆን አለበት። 

ቤት ማሳደስ -

DHCD ብቁ ለሆኑ አስፈላጊ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ቤቶች ላላቸው የአንድ ቤተሰብ የቤት ባለቤቶች በዲ.ሲ. የቤቶች ኮድ ስታንዳርድ ኮድ እኩል ለማድረግ የተለያዩ የዕርዳታ ፕሮግራሞች ይሰጣል።  DHCD እስከ $75,000 የሚደርስ ለቤት ጥገና ብድር እና ዕርዳታ ይሰጣል። የገንዘብ ዕርዳታው የዲ.ሲ. የህንጻዎች ኮድ ጥሰቶችን፣ ለጤና እና ለደህንነት አስጊ ሁኔታዎችን እንዲሁም ጣርያ ለማደስ እና አዲስ ለማስገባት ለመሳሰሉ ችግሮች ላይ ይውላል።    DHCD የቤት ባለቤት የሆኑ አዛውንቶችን በዚህ ፕሮግራም አማካይነት ወደ ቤታቸውን በቀላል መንገድ ለመግባት እንዲችሉ ይረዳቸዋል።   በተጨማሪም DHCD ብቁ ሆነው ለተገኙ የቤት ባለቤቶች እና ቤት አሠሪዎች ከ1978 ዓ.ም. በፊት ለተሠሩ የሌድ ቀለም የተቀቡ ቤቶች  ከሌድ ነጻ ለማድረግ በአንድ ቤት እስከ $17,500 ዕርዳታ ይሰጣል።   የዋሽንግተን ከሌድ ነጻ ፕሮግራም፣ ለምሳሌ፣ የቤቱ ቀለም ከሌድ ነጻ መሆኑን ለመመርመር ይረዳል።   ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ለመሆን የቤቱ ባለቤት ወይም ተከራይ ገቢው ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ መሆን አለበት።   ንበረቶቹ ከ6 ዓመት በታች የሆነ ልጅ የሚኖርበት ወይም የኪራይ ቤት ከሆነ ደግሞ ከ6 ዓመት ዕድሜ በታች የሆነ ልጅ ያላቸው ቤተሰቦች መኖር አለባቸው።  እርጉዝ የሆኑ ሴቶች የሚኖሩባቸው ዩኒቶችም ለዕርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የቤት ባለቤትነት ፕሮግራሞች

የዲስትሪክቱ የቤት ባለቤትነት ፕሮግራሞች ለዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ለሚገዙ ቤተሰቦች እና የዲስትሪክቱ የመንግሥት ሠራተኞች የገንዘብ ዕርዳታ ይሰጣሉ።  የቤት መግዛት ዕርዳታ ፕሮግራም (HPAP) ብቁ ለሆኑ አመልካቾች ከወለድ ነፃ የሆኑ ብድሮች እና የመዝጊያ ዋጋ ዕርዳታ በመስጠት ለአመልካች የመኖሪያ ቤቶች፣ ኮንዶሚንዬሞች ወይም የህብረት ቢቶች የመግዛት ዕድል  ይሰጣል።   የብድሩ መጠን የሚተመነው በቤተስብ ገቢ፣ ቁጥር፣ እና እያንዳንዱ አመልካች ለቤቱ ግዥ በሚያወጣው ገንዘብ ነው።  ብቁ የሆኑ አመልካቾች እስከ $40,000  ለቤቱ መግዣ ክፍተት የብድር ዕርዳታ እና ተጨማሪ $4,000 የመዝጊያ ዕርዳታ ያገኛሉ።  የHPAP 0% የብድር ወለድ ለመጀመሪያው አምስት ዓመት ሳይከፈል ይተላለፋል እና በ40 ዓመታት ውሥጥ ይከፈላል።  

የቤት ምክር

DHCD በተለያዩ የማህበረሰብ ድርጅቶች አማካይነት ለተከራዮች፣ የወደፊት ቤት ገዥዎች እና አሁን የቤት ባለቤት ለሆኑ ሰዎች የምክር አገልግሎት እና ሥልጠና ይሰጣል።   ርዕሶቹ በባንክ ከመወሰድ ማስቆም፣ የግል ክሬዲት አያያዝን፣ ለፕሮግራም ዕርዳታ ማመልከት፣ የቤት አገዛዝ ሂደት አያያዝን፣ የቤት ባለቤትነት ሥልጠና፣ አፓርትመንት አፈላለግ እና ሌሎች የኗሪዎች የቤት ፍላጎቶች አገልግሎቶችን የተመለከቱ ዕርዳታዎችን ያካትታሉ።  በተጨማሪም ተከራዮች መብታቸውን እና ኃላፊነታቸውን፣ የወደፊት መፈናቀልን፣ የኪራይ/የመባረር ምክር እና የአፓርትመንት አያያዝን የተመለከቱ አገልግሎቶችን ይሰጣል።  ዕርዳታዎቹ ወሩን በሙሉ በተከታታይ ይሰጣሉ።  በአካል አንድ ለአንድ ምክር በቀጠሮ ይሰጣል። 
በባንክ ከመወረስ መከላከያ መረጃዎች  – DHCD በተለያዩ የዲ.ሲ. ማህበረሰብ ድርጅቶች በክፍያቸው ወደኋላ የቀሩ የቤት ባለቤቶችን ወይም ቤታቸው በባንክ ሊወሰድባቸው የሆኑትን የቤት ባለቤቶች የምክር አገልግሎቶች ይሰጣል።  በተጨማሪም DHCD በባንክ የመዘጋት ጉዳይ ከአጭበርባሪዎች እንዴት መጠንቀቅ እና በባንክ ቤት ስለመወረስ ሁኔታ የተከራዮችን መብት የተመለከቱ መረጃዎችን ይሰጣል። 

የአካባቢ መሻሻል

የDHCD ዋና ተልዕኮ አካባቢዎችን ማሻሻል ነው።  አብዛኞቹ የመሥሪያ ቤቱ ፕሮግራሞች አካባቢዎችን ለማጠናከር እና ለማሻሻል የታቀዱ ናቸው።  .

የትናንሽ ንግዶች ቴክኒካል ዕርዳታ

DHCD በተለያዩ ከቀረጥ ነፃ በሆኑ የማህበረሰብ ድርጅቶች አማካይነት ብቁ ለሆኑ የኮሎምብያ ዲስትሪክት የንግድ አካባቢዎች ለትናንሽ እና የችርቻሮ ንግዶች የዕርዳታ አገልግሎት ይሰጣል።  የሚሰጡት ዕርዳታዎች የሚከትሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦ የማይክሮ ብድር ፓኬጂንግ፣ የንግድ ፕላን፣ የንግድ ሥልጠና፣ በግል የንግድ ቴክኒካል ዕርዳታ፣ የቀረጥ ማዘጋጀት ዕርዳታ፣ የሂሳብ ዕርዳታ፣ ወይም የህግ ዕርዳታ።  በተጨማሪም የጋራ የንግድ ዕርዳታ እንቅስቃሴዎችን፣ እንደ የንግድ ሕብረት ማቋቋም፣ የንግድ ኮሪደሮች ማስፋፋት፣ በብዛት መገብየት፣ ከብዛት ቅናሽ የማድረግ ጥረት፣ እና የጋራ ቦታ አስተዳደርን ይገፋፋል።  ማንኛውም የንግድ ድጋፍ እንቅስቃሴ የአካባካቢውን ንግዶች የሚያንሠራራ እና ወጪያቸውን በቀጥታ ሳይሸፍን ዕድገታቸውን የሚገፋፋ ለድጋፍ ብቁ ይሆናል።  በዚህ ፕሮጋራም የሚሳተፉ ለትርፍ የማይሠሩ የማህበረስብ ድርጅቶች በመላው በዲስትሪክቱ ይገኛሉ።     

የሱቆች የፊትለፊት ገጽታ መሻሻል

በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ ከዝቅተኛ/መካከለኛ ገቢ ያላቸው የችርቻሮ/የንግድ አካባቢዎች ሱቆች የፊትለፊት ገጽታ መሻሻል ፕሮጀክቶች የሚሠሩት ብቁ በሆኑ ለትርፍ የማይሠሩ የማህበረሰብ ድርጅቶች ነው።   ለትርፍ የማይሠራው ድርጅት ለንገዱ እና/ወይም ለንብረቱ ባለቤት የፊት ለፊት ማሻሻያ የባለሞያ የንድፍ እና የጥገና አገልግሎቶች ይሰጣል።  በታቀደው አካባቢ ብቁ ሆነው የተገኙ የንግድ እና/ወይም የንግድ ንብረት ባለቤቶች ለአጠቃላይ ጥገና እና በሮች፣ መስኮቶች፣ ምልክቶች፣ ግርዶሽ፣ መብራት ለማስገቢያ የሚሆን ተመሳሳይ ዕርዳታ ያገኛሉ። 

አድልዎ የሌለበት መኖሪያ ቤት

አድልዎ የሌለበት መኖሪያ ቤት ፕሮግራም ለሁሉም በእኩልነት አድልዎ የሌለው የመኖሪያ ቤት የማግኘት ዕድልን ማስፋፋት እና የአካባቢ እና የፌደራል አድልዎ የሌለው ቤት ማግኘት ሀጎችን፣ ድንቦች እና ድንጋጌዎች በማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የቤት ሠሪዎችን እና በDHCD በኩል ለፕሮግራም እና ለፕሮጀክት ገንዘብ የሚቀበሉ የግል ነዋሪዎች  መከበሩን ማረጋገጥ ነው።   DHCD ለከተማ ኗሪዎች —እንደ የኢሚግራንት ማህበረሰቦች፣ አካለ ስንኩሎች እና አዛውንቶች— ቤት የመከራየትም ሆነ የመሸጥ አፈጻጸምን በተመለከተ አድልዎ ስለሌለው የቤት መብታችው ትምህርት ይሰጣል።  ይህ ፕሮግራም ለትርፍ ለማይሠሩ ድርጅቶች እና ደንበኞቻቸው ቁሳቁስ እና በቦታው በመገኘት ትምህርት ይሰጣል።.

የሴክሽን 3 ፕሮግራም

የ1968 የሴክሽን 3 የቤቶቸ እና የከተማ ልማት ድንጋጌ፣ ሴክሽን 3 ለዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የዲስትሪክቱ ኗሪዎች ጥቅማጥቅሞች ተብሎ  የሚጠራው ድንጋጌ ለኗሪዎች በርካታ በሆኑ የDHCD የግንባታ ሥራዎች የተሰማሩ ተዋዋዮች እንዲቀጠሩ ዕድል ይሰጣቸዋል።   ሴክሽን 3 ማንኛውም  የፌደራል ገንዘብ የሚቀበል ከDHCD ዕርዳታ የሚያገኝ በተቻለው መጠን በየአካባቢያቸው ላሉ ፕሮጀክቶች ወይም እንቅስቃሴዎች  የሥራ ሥልጠና፣ ሥራ እና የኮንትራክት ዕድል ለዝቅተኛ ወይም በጣም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ኗሪዎች  እንዲሰጡ ይጠይቃል።  ንግዶች ለንግዶች ጉዳይ ሴክሽን ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እንዲሁም የመቅጠር፣ የሥልጠና እና የኮንትራት ዕድል ሊኖራቸው ይችላል። 

ንብረት መግዛት እና ማስወገድ (PADD) – ይህ ፕሮግራም በዲስትሪክቱ ውስጥ ሰው የሌለባቸውን እና ባለቤት የሌላቸውን የመኖርያ ንብረቶችን ቁጥር በመቀነስ አካባቢዎችን ማጠናከር እና ሰው የሌለባቸውን እና ባለቤት የሌላቸውን የመኖርያ ንብረቶች አሻሽሎ ማንኛውም ዓይነት ገቢ ላላቸው የዲስትሪክቱ ተቀማጮች የመኖሪያ ንብረቶች እንዲያገኙ ያደርጋል።   ይህንንም የሚያደርገው የንብረት ባለቤቶችን ባዶ ቦታ እና የተጣለ የመኖርያ ንብረታቸውን እንዲያድሱ እና/ወይም እንዲኖሩበት መገፋፋት፣  ባዶ ቦታ እና የተጣለ የመኖርያ ንብረቶቹን በድርድር መሸጥ፣ ወይም ባለንብረቶች ንብረቱን ለማሳተዳደር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ወይም ችሎታ ሳይኖራቸው ሲቀር መንግሥት ለሕዝብ እንዲጠቀምበት ማድረግ፣ በስጦታ ወይም በባንክ ዕዳ ታክስ መሸጥ፣ ንብረቶቹን ለግለስቦች ወይም ቤት አሠሪዎች አሳድሰው ወደ ምርጥ የሆኑ  መጠነኛ ዋጋ ያላቸው የሽያጭ የአንድ ቤተሰብ እና/ወይም የብዙ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች እንዲያደርጉት መሸጥ ነው።  እነኝህን ቦታዎች ለመግዛት የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ንግዶች የግዥ ድርድር በማድረግ፣ በDHCD የተዘጋጀ ሎተሪ፣ ወይም በ DHCD የተዘጋጀ የንብረት ሀራጅ ማግኘት ይችላሉ። 

የማስተርጎም አገልግሎቶች:

ስለ የቤት ባለቤትነት እና ስለማሳደስ፣ የመኖርያ ቤት እና የኮንዶ ህጎች እንዲሁም የማሻሻያ ገንዘብ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጥያቄ ካለዎት በቢሮ ስልክ ቁጥራችን (202) 442-7200 ይደውሉልን።  ስልክ ከደወሉልን ወይም ወደ ቢሮአችን ከመጡ በአካል አስተርጓሚ እንዲያገኙ ከሠራተኞቻችን አንዱ ይረዳዎታል።  
አድራሻ:

DC Department of Housing and Community Development
1800 Martin Luther King Jr. Ave. SE
Washington, DC 20020
202-442-7200
www.dhcd.dc.gov